በሀረሪ ክልል “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 17ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬው ዕለት ይከበራል፡፡
ዘንድሮ በክልል ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በክልል ደረጃ በድምቀት ይከበራል።
ዛሬ ከረፋዱ 4:30 ሠዓት ላይ በሀረሪ ክልል በሚገኙ ሁሉም መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም ተከብሮ ይውላል።