በሀረሪ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ ግብር የታደሱና የተገነቡ 4 የአቅመ ደካማ ወገኖች መኖሪያ ቤቶች ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ታላልፎ ተሰጠ
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በክረምት በጎ ፍቃድ ስራ በ3 ወረዳዎች የአቅመ ደካማ ወገኖች የታደሱና የተገነቡ 4 የመኖሪያ ቤቶችን በማስመርቅ የሐረር ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሮዛ ኡመር በተገኙበት ለተጠቃሚዎች ርክክብ አደርጉዋል።
መኖሪያ ቤቶቹን መርቀው ያስተላለፉት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለቀጣዩ ትውልድ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ለማውረስ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ምቹ መኖሪያን በመፍጠር የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች የሚያቃልሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።