በሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሳዊ አገልግሎት አባላት በሀረር ከተማ አራተኛ የገብርኤል በአል የሚከበርበትን ስፍራን አፅድተዋል።
በሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሳዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ግሩም ውብሸት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሳዊ አገልግሎት አባላት ጋር በመተባበር በሀረር ከተማ አራተኛ የሚገኘው የቁልቢ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በአል የሚከበርበትን ስፍራ ማፅዳታቸውን ገልፀዋል።
በተመሳሳይም የሰላም አደረጃጀቶቹ በሀረር ከተማ አራተኛ የሚገኘው መስጊድ ጁማአ የሚሰገድበትን ስፍራንም በጋራ አፅድተዋል።





የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሳዊ አገልግሎት ሰጪ አባላት በክልሉ በከተማና ገጠር በሚከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ በንቃት እየተሳተፉ መሆናቸውንም ምክትል ኮማንደር ግሩም ገልጸዋል።
የሀኪም ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር አብዲ ኢብራሂም በበኩላቸው የወረዳውን ህ/ሰብና አደረጃጀቶችን በማስተባበርና በማሳተፍ በወረዳው የተጠናከረ የሰላምና የፀጥታ ጥበቃ ስራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
በፅዳት ዘመቻ መርሐ-ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽ እና የሀኪም ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አባላትን ጨምሮ የተለያዩ የሰላም አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።