በሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ “የመስቀል ደመራ በዓል በማስመልከት የፅዳት መርሃ ግብር ተከናወነ

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች ፣የፖሊስ ኮሚሽን አባላት ፣የወረዳ ሰላም አደረጃጀቶች፣ የሀይማኖት አባቶች በጋራ በመሆን የሀረርን የአብሮነት እሴት በሚገልፅ መልኩ የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በሚከበርበት ቦታ የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

በዚህ የጽዳት ዘመቻ ላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ከሙስሊም እምነት አባቶችና ወንድሞች ፣ከፕሮቴስታንት እምነት አባቶች በጋራ የመስቀል ደመራ በአል ሀይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ በቀጣይም ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በትብብር በመስራት የክልላችን አንዱ ድምቀት የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት በማስተላለፍ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን

መስከረም 15/01/2017

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top