በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝብን ከአደጋ እና ስጋት የመጠበቅ፣ የህግ የበላይነትን ከማስፈን አንፃር ከፖሊስ ኮሚሽን ፣ከወረዳ ፀጥታ አስተባባሪዎች ፣ የወረዳ የሚሊሻ ዲስክ የወረዳ ጣቢያ አዛዦች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል በመርሃ ግበሩ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እና የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን የተገኙና በቀጣይ መሰራት ያለባቸውን የህግ ማስከበር ስራዎች በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ የተሰጠበት ውይይት ነበር ።
በተለይ ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ግለሰቦችን ፣ፀጉረ ልውጦችን በትኩርት በመለየት ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን በማለት የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ለፀጥታ አካሉ በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡
ሰላም ለሁሉም!!!
ሁሉም ለሰላም!!!