በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ10ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ወጣቶች የሽኝት መርሃ ግብር ተደረገ

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ10ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ወጣቶች የሽኝት መርሃ ግብር ተደረገ

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ10ኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ ወጣቶች የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሽኝት መርሃ ግብር አደረገ፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ የ10ኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች በነበራቸው ቆይታ ላደ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሙያዊና በጉልበት የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በማበርከት ሀገር የጣለባችሁን አደራ በሙሉ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ፍላጎትና ተነሣሽነት መፈፀማቸውን ገልፀው ወጣቶቹ ላበረከቱት በጎ ሥራዎች ምስጋና በማቅረብ በሄዱበት ቦታ ሁሉ የሀረሪ ክልል የሰላም አምባሣደሮች እንዲሆኑና በተሰማሩበት ስራ ሁሉ በውጤታማነት እንዲወጡ በማለት መልእክት ምክር አዘል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር ነስሪ ዘካሪያ በበኩላቸው በቆይታ ጊዜያቸው ላደረጉት በጎ ስራ በማመስገን የ10ኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች በሄዱበት ቦታ ሁሉ ሀረርን የሰላም የመቻቻል ፣የአብሮነት ፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት እና የመራዳዳት ሀገር መሆኗን እንዲያስምሩ በቆይታቸው ሀረር ላይ ያገኙትን ልምድ በሚሄዱበት ቦታ እንዲያሳውቁና በሚሰማሩበት ስራ መልካም እንዲገጥማቸው ተመኝተው የምስክር ወረቀት በመስጠት መርሃ ግብሩ የተጠናቀቀ ሲሆን የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማኔጅመንት አባላትና የሰላም እሴት ባለሞያዎች ተሳትፈዋል ፡፡

+7

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top