በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ሐኪም ወረዳ፣ አሚር ኑር ወረዳ ፣አባድር ወረዳ ፣ ድሬ ጠያራ ወረዳ ፣ ሸንኮር ወረዳ እና ኤረር ወረዳ የአብሮነት ቀን ተከብሯል

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ሐኪም ወረዳ፣ አሚር ኑር ወረዳ ፣አባድር ወረዳ ፣ ድሬ ጠያራ ወረዳ ፣ ሸንኮር ወረዳ እና ኤረር ወረዳ የአብሮነት ቀን ተከብሯል
በሐኪም ወረዳ፣ አሚር ኑር ወረዳ ፣አባድር ወረዳ ፣ ድሬ ጠያራ ወረዳ ፣ ሸንኮር ወረዳ እና ኤረር ወረዳ በህዝቦች መካከል አብሮነትን በማጠናከር ሐገረ መንግሰት ግንባታን ለማስቀጠል እዲያስችል ከላይ በተጠቀሱትአምስት ወረዳዎች የአብሮነት ቀን ተከበረ።
የአብሮነት ቀን በሀረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችን እና ለድጋፍ የተመደ ባለሞያዎችና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት የወረዳ የሰላም ቤተሰቦች፣ የወረዳው ነዋሪዎች ፣የወረዳው መንግሥት ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ።
በቦታው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላምናፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አመራሮች የአብሮነት ቀን ስናከብር በመተሳሰብና አብሮነታችን በማጠናከር አቅመ ደካሞችን በመርዳት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
አያይዘውም የዛሬውን ቀን ስናከብር ህብረ ብሔራዊ አንድነትታችን ድምቀታችንና ውበታችን ጭምር ነው ብለን ሲሆን ÷የዛሬው ትውልድም ልዩነቶቹን በማጥጠብ፣አንድነቱን በማጠናከር ህብረ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ እሴቶችን በማዳበር ለሀገር ብልፅግና ሊሰራ እንደሚገባ አፅንኦት በመሥጠት ያስተላለፉ ሲሆን በቀጣይም ማህበረሰቡና የሰላም አደረጃጀቶቻችን ጠንክረው ለሰላም ዘብ መቆምና ባለቤት መሆን እንዳለባቸውም ቃል የተገባበት መድረክ ነበር።
ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን ክፍል ነው።
ነሐሴ 22/2016
+15
All reactions:

Mohammed Sule Oumer, Fahmi Sufiyan Ibro and 78 others

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top