በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጥምር የፀጥታ ኮሚቴ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ተወያየ

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ አካሉ በቅንጅት በመሥራት በክልላችን የተከበረውን ሀይማኖታዊ የመስቀል ደመራ በአል በሰላም መጠናቀቅ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ለተሰራው ሥራ ምስጋና የተሰጠበትና በቀጣይም በክልላችን ብሎም በከተማችን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ የፀጥታው ጥምር ኃይል ከወትሮው በበለጠ መሥራት እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠሲሆን በመድረኩ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እና የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሀላፊ ምክ/ኮሚሽነር ገናነው ጥበቡ በመገኘት በተለይ ከአራተኛ መስኪድ ጋር ተያይዞ ያለ በሀማህበረሰቡ ውስጥ የፅንፈኝነትና የአክራሪነት መርዝ የሚረጩና ለክልላችን የሰላም ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን በመለየት የህግ የበላይነት እንዲከበር የፀጥታ አካሉ በቅንጅት መሥራት እንዳለበት የሥራ መመሪያና አቅጣጫ ተሰጥቷል ተሣታፊዎችም በዚህም የፌደራል ፖሊስ ፣ከምስራቅ እዝ ፣የብሄራዊ መረጃ ደህንነት ፣ የፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና ከሁሉም ወረዳዎች የጣቢያ አዛዦች በስፋት ውይይት የተደረገ ሲሆን ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ጥበቃዎችን በማጠናከር ፍተሻዎች በየኬላዎች በጥንቃቄ መሰራት እንዳለበት ፣ ድንገተኛ የፓትሮል ጥበቃዎች ከማህበረሰቡና ከኃይማኖት አባቶች ጋር በመወያየት ለተከታዮቻቸው በቂ ግንዛቤ መስጠት እንደሚገባ ከሀይማኖት ፅንፈኝነት ጋር ተያይዞ አገር ጠል የሆኑ ግለሰቦችን በትኩረት ማጋለጥ ፣ፀጉረ ልውጦችን በንቃት በመከታተል ማጋለጥ ፣ወቅታዊ መረጃ በመለዋወጥ በተለይ የፀጥታ ኃይሉ የሰላም አደረጃጀቶቻችንን ማንቀሳቀስ እንደሚገባ ጥብቅ የስራ አቅጣጫ እና የሥራ መመሪያ የተሰጠበት መድረክ ነበር።

ሰላም ለሁሉም!!

ሁሉም ለሰላም!!

ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top