በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ከፀጥታው አካል ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በክልላችን አንፃራዊ ሰላምን ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሸጋገር የፀጥታው አካል በቅንጅት መስራት እንዳለበት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በመርሃ ግብሩ በመገኘት በክልላችን እየተሰሩ ላሉ የልማት ስራዎች ዘላቂነት ያለው ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑንና የፀጥታው አካል በመቀናጀት በያገባኛል ስሜት ስራዎች መስራት እንዳለባቸው እና የሰላም አደረጃጀቶቻችንን በማጠናከር ማህበረሰቡ የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን መሥራትና ከአጎራባች ወረዳዎች ጋርም በጋራ በፀጥታ ሥራ በመቀናጀት እንዲሰራና ሊከተሏቸው የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎችን አብራርተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩም የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣንና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሓላፊ ምክትል ኮሚሽነር ገናነው ጥበቡ ስለ ፀጥታው ስራ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አላማ አስፈፃሚዎች እና ዳይሬክተሮች የፌዴራል ፖሊስ ፣የምስራቅ እዝ ተወካዮች የብሔራዊ ደህንነት እና የወረዳ ጣቢያ አዛዦች ፣የወረዳ የሰላምና ፀጥታ አስተባባሪዎች ፣የሚሊሻ ዲስክ በውይይቱ ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ሰላም ለሁሉም!!!!

ሁሉም ለሰላም!!!!

ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን

All reactions:

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top