በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአላማ አስፈፃሚ፣ ተጠሪ ተቋማት በጋራ የአንደኛውን ሩብ አመት አፈፃፀም ገመገመ================
ጥቅምት 7/02/2017
በሰላምን ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 አንደኛው ሩብ አመት ”አንድ እቅድ”’ አንድ ሪፖርት” የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ፣የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አላማ አስፈፃሚዎች ፣ደጋፊ ዳይሬክተሮች በተገኙበት የ2017 ዓ.ም . ሪፖርት አፈፃፀም የካፒታል ፕሮጀክት አፈፃፀም በተጠሪ ተቋማት በኩል ያለበት ደረጃ የቀረበና የታየ መሆኑ
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በግምገማው ላይ ሁሉም ድርሻውን መወጣት እንዳለበት
በተለይ ”’አንድ እቅድ ””አንድ ሪፖርት””መሠረት መፈፀም እንዳለበትና በቀጣይ የፖሊስ ኮሚሽን ያሉትን ክፍተቶች በማስተካከል ወደ ሶፍትዌር እንዲገባ መደረግ እንዳለበት አስፈላጊው ሞያዊ ድጋፍ በእቅድ/ዝ/ክ/ ክፍል በኩል እንዲደረግ
በተጨማሪም ተጠሪ ተቋማት በየአስራ አምስት ቀኑ ””አንድ እቅድ”” አንድ ሪፖርት”’ ያለበትን ደረጃ መገምገም በቃለ ጉባኤ በምስል መረጃ መያዝ እንደሚገባ እንዲሁም የሱፐርቨዥን ቡድን በጋራ ወደታች በማውረድ የሚታዩ ክፍተቶችን እያረሙ መሄድ እንደሚገባ በቀጣይ የሁለተኛው ሩብ አመት እንዲስተካከል አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን
ተሳታፊዎችም በቀጣይ የተነሱ ክፍተቶችን በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በመደጋገፍ መንፈስ እንሰራለን በማለት በመግባባት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ሰላም ለሁሉም!!!!
ሁሉም ለሰላም!!!
ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን