በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀገር መከላከያ ስራዊት የ2017 የ1ኛ ዙር መደበኛና ሙያተኛ ምልመላ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄደ

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀገር መከላከያ ስራዊት የ2017 የ1ኛ ዙር መደበኛና ሙያተኛ ምልመላ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄደ

ጥቅምት 13/2017

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 የመደበኛና የሙያተኛ የአንደኛው ዙር የምልመላ እቅድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በመርሃ ግብሩ የሐረሪ ክልል ብልጽግና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብድልሃኪም ኡመር እና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ የተገኙ ሲሆን የምልመላ እቅዱንና የ2016 የየወረዳዎችን አፈፃፀም ፣የነበሩ ጠነሰካራ ጎኖችና የነበሩ ክፍተቶችን በስፋት ያቀረቡት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በእቅዱ ዙሪያ ትኩረት ተሰጥቶበት እንዲሰራና ለወረዳዎች በተሰጠው ኮታ መሠረት ለመደበኛና ለሙያተኛ በተለይ በኢንጅነሪንግ፣በጤና፣በህግ፣በምህንድስና፣በግዥና ፋይናንስ፣በንብረት አስተዳደር ፣ በኪነጥበብ፣የትራንስፖርት ማኔጅመንት እና በተለያዩ ሞያዎች የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅቱን በመግለፅ ሁሉም የወረዳ አመራሮች በትኩረት የክልላችን ወጣቶች በዚህ የሥራ እድልና ሀገር የመገንባት ስራ ላይ እንድታሳትፉ በማለት የገለፁ ሲሆን

የሐረሪ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ አብዱላኪሞ ኡመር በበኩላቸው ለሰንደቅ አላማችን ክብር የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን በሰው ሀይል መገንባት ሀገር መገንባት ነው

ኮሎ/ዮናስ ሮባ የብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል የድሬዳዋ አስተዳደር እና የሐረሪ ክልል ጽ/ቤት ሀላፊ እንደሀገር ያለውን የምልመላ ውጤት የሀረሪ ክልል በ2016 በሁለቱም ዙር ወደማሰልጠኛ በማስገባት በጥሩ ውጤትና በአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቁን ገልፀው በ2017 የአንደኛው ዙር ምልመላ ስራ ጠንክራችሁ ደረጃችሁን ሣትለቁ ወጣቱን እንድታሰልፉ በማለት መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን

ተሳታፊዎችም በቀረበው እቅድ ሀሳብ በመሥጠት በተለይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በማዘጋጀት ማህበረሰቡን ማወያየት ወጣቱን የዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆን እንሰራለን በማለት እና በወቅታዊ የክልሉ የፀጥታ ጉዳይ ላይም ውይይት በማድረግ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top