በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአንደኛው ሩብ አመት የሪፖርት አፈፃፀምና የ11ኛው ዙር የብሄራዊ በጎ ፍቃድ ወጣቶች ምዝገባ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ተገመገመ

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአንደኛው ሩብ አመት የሪፖርት አፈፃፀምና የ11ኛው ዙር የብሄራዊ በጎ ፍቃድ ወጣቶች ምዝገባ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ከቢሮ የማኔጅምንት ፣ቡድን መሪዎች እና የዘጠኙም ወረዳ የፀጥታ አስተባባሪዎች ፣የሚሊሻ ዴስክ በጋራ በመሆን ተገመገመ ፡፡

በአንደኛው ሩብ አመት የተሰሩ ስራዎች ያጋጠሙ ችግሮችና የወደፊት አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ነስሪ ዘከርያ የወረዳዎችን ሪፖርት በማዳመጥ ግብረ መልስ የተሰጠበት መድረክ ነበር ፡በዚህም በተለይ ‘’አንድ እቅድ” “ አንድ ሪፖርት” በሚለው መመሪያ መሰረት የታየ ሲሆን የ11ኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች ምዝገባ በተሠጠው ቀን መሰረት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራና የቀረበው የ1ኛው ሩብ አመት እቅድ አፋፀምም በቀጣይ በተሠጠው ግብረ መልስ መሰረት ሁሉም ወረዳ ማስተካከል እንዳለበት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ አቅጣጫ እና የስራ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል፡፡

ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን

መስከረም 22/2017

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top