በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የዘጠኙም ወረዳ ሚሊሻ ዲስክና የሚሊሻ ባለሞያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሁሉም ወረዳዎች ሚሊሻ ዲስክና የሚሊሻ ባለሞያዎች ጋር በ2017 እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ የነበሩ ጠንካራና የነበሩ ክፍተቶች የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በተገኙበት የተገመገመና እስከ አሁን በሰላምና በልማት ያገኘናቸውን ድሎች በመያዝ የክልሉን አስተማማኝ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መላው የሚሊሻ ኃይል ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይገባል በሚል እና ሊከተሏቸው የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎችን አብራርተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሚሊሻ ጽ/ቤት ሃላፊ ኮሚሽነር አድናን አህመድ በቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራርን ከውስጥና ከውጭ ከአጎራባች የምስራቅ ሐረርጌ ወረዳና ማያ ሲቲ ጋር በፀጥታ ዙሪያ በማጠናከር በቅንጅት በመስራት እና የክልላችንን ሰላም ማስጠበቅ ይገባል ሲሉ የስራ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን በመርሃ ግብሩ የሚሊሻ ጽ/ቤት ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በተሰጠው የስራ አቅጣጫ በመግባባት ተጠናቋል።

ሰላም ለሁሉም!!!!

ሁሉም ለሰላም!!!!

ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን

+3

All reactions:

110Hasan Adam, Ahmed Mohammed Abdukrim Ali and 108 others

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top