በሰላምና ፀጥታ እስተዳደር ቢሮ ከክልሉ የመጅሊስ አመራሮችና ከኃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ውይይት ተደረገ=========================
ጥቅምት 3/2017
በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከክልሉ የመጅሊስ አመራሮች ፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ከሁሉም ወረዳ የጁምአ መስኪድ ኢማሞች፣ሼኮች ፣አባገዳዎች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እና በአራተኛ መስኪድ ተፈጥሮ የነበረው ችግር መንስኤና በሰላም መጠናቀቅ ላይ ያተኮረ ውይይት በስፋት የተደረገ ሲሆን በመድረኩም የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ ፣ የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ኃላፊ አቶ አዪብ አህመድ እና የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን የተገኙ ሲሆን አቶ ቶፊቅ መሀመድ ሁሉም ቤተ እምነቶች ስለ ሰላም ፣አብሮነትና መቻቻልን ፣ስለ ክልላችን ልማት ለተከታዮቻቸው ማስተማር እንዳለባቸውና በቀጣይ በወንድማማችነት ፣በመቻቻል ፣በአብሮነት መሥራት እንደሚገባ እንዲሁም በመስጂዶቻችን አስተምህሮቱ መሆን ያለበት ሀይማኖታዊ እሴቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ መተላለፍ እንዳለበት ኡለማዎቻችን በትኩረተሰና በጥንቃቄ ማስተማር እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ የተቀመጠበት የማያግባቡ ጉዳዮች ቢፈጠሩ እንኳ ከመስጂድ ውጪ በሚዘጋጀው መድረክ መወያየት እንደሚገባ ፣አስተምህሮና ተግባራዊ ህይወትን ማስማማት ፣በሰላም አብሮ ለመኖር እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ፣የሰላምና የአብሮነት አመለካከት ማጎልበት በሚሉ ሀሳቦች ገንቢ ሚና ለመጫወት ሁሉም በቁርጠኝነት መቆም እንደሚገባ ተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት በመስጠት ፣የህግ የበላይነትም መከበር እንዳለበት በተለይ ኃይማኖቱን ለመከፋፈል የሚጥሩ ጥቂት ግለሰቦች ተለይተው ሊጠየቁ እንደሚገባ የክልሉ መጅልስም ድርሻውን መወጣት እንዳለበት መሲጂዶቻችን ሰላምና ሰላም ብቻ ማወጅ እንደሚገባ ፣ በሁሉም ጁምዓ መስጂዶቻችን ተመሣሣይ ”ቁጥባ ” መተላለፍ እንዳለበት በመግባባት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ሰላም ለሁሉም!!!
ሁሉም ለሰላም!!!
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን





All reactions:
116Ahmed Mohammed Abdukrim Ali, Fahmi Sufiyan Ibro and 114 others