በድሬ ጠያራ ወረዳ የመጣዉን ሰላም ማስቀጠል የሁሉም ሐላፊነት እንደሆነ ተገለፀ

በድሬ ጠያራ ወረዳ የመጣዉን ሰላም ማስቀጠል የሁሉም ሐላፊነት እንደሆነ ተገለፀ

በሐረሪ ክልል ድሬጠያራ ወረዳ የተመዘገበዉ የሰላም እንቅስቃሴ ስራ ለሰሩ የወረዳዉ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት እዉቅና የመስጠት ስነ-ስርአት በዛሬዉ እለት አከናዉኗል።

በፕሮግራሙም ላይ የሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሐላፊ አቶ ቶፊቅ መሐመድ የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ረመዳን ጂብሪል የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚኒቲ ፖሊሲንግ አደረጃጀት አባላትና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ተካፋይ ሆነዋል።

በእለቱ ንግግር ያደረጉት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሐላፊ እንደተናገሩት ወረዳዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እያስተናገደ እንደሚገኝ ገልፀዉ ለዚህም የአካባቢዉ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን በበኩላቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት የሰላም ጉዳይ በአንድ አካል ብቻ የሚተዉ ሳይሆን የሁሉም ሰዉ በመሆኑ ሁሉም የወረዳዉ ነዋሪ የአካባቢዉን ሰላም ከፖሊስ ጎን በመቆም ማስቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለወረዳዉ ሰላም የበኩላቸዉን አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት እና ግለሰቦች የዕዉቅና ምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

መስከረም 19/1/2017

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top