በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በሀኪም ወረዳ ከሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሰላም አደረጃጀቶችና ከወረዳው ማህበረሰብ ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እና በአራተኛ መስኪድ ተፈጥሮ የነበረው ችግር መንስኤና በሰላም መጠናቀቅ ላይ ያተኮረ ውይይት በስፋት የተደረገ፡፡
በመርሃ ግብረቱ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ ፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ነስሪ ዘከርያ እና የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ኃላፊ አቶ አዪብ አህመድ የተገኙ ሲሆን
ውይይቱን ያስጀመሩት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ ሀረር በአለም ደረጃም ሆነ በሰላም ፣በአብሮነትና በመቻቻልም መልካም ስም ያላት መሆኑን ገልፀው ይህን መልካም ስም አጠናክሮ ከማስቀጠል አንፃር የሐይማኖት መሪዎች፣የወረዳው ማህበረሰብ በትኩረት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል በማለት የገለፁ ሲሆን ፡፡
የሐይማኖት መሪዎችም ሆነ ቤተ እምነቶች ሁሌም ማስተማር ያለባቸው ሰላምና አንድነት መሆን እንዳለበትና በንቃት የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ የኮሪደር ልማት ስራዎችን መደገፍ የወል ግዴታችን ነው በማለት ብዝሀነታችን ውበታችን እና አንድነታችንን የምናጠናክርበት ሊሆን ይገባል እንጂ የግጭት ምንጭ ሊሆን አይገባም በማለት
በሰላም አብሮ ለመኖር እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ፣የሰላምና የአብሮነት አመለካከት ማጎልበት ገንቢ ሚና ለመጫወት ሁሉም በቁርጠኝነት መቆም እንደሚገባ ተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት በመስጠት በእንደዚህ መልኩ ተቀራርቦ የመወያየት ባህልም ሊጠናከር እንደሚገባ
በተለይ የህግ የበላይነትም መከበር እንዳለበት ችግር ካለም በሰከነ መንገድ በውይይት በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበርና ኃይማኖቱን ለመከፋፈል የሚጥሩ ጥቂት ግለሰቦች ተለይተው ሊጠየቁ እንደሚገባ ማህበረሰቡም ድርሻውን መወጣት እንዳለበት መሲጂዶቻችን ፣ቤተክርስቲያኖቻችን ቸርቾቻችን ሰላምና ሰላም ብቻ ማወጅ እና ማስተማር እንደሚገባ መግብብት ላይ የተደረሰና በቀጣይ አቅጣጫ በመግባባት ተጠናቋል
ሰላም ለሁሉም!!!
ሁሉም ለሰላም!!!
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን


