የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም በክልሉ የምግብ ስርዓትና ስርዓተ-ምግብ ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ተወያይቶ አፅድቋል።
በተለይም ደንቡ በአመጋገብ ሥርዓት የሚደርሰውንና በምግብ መዛባት ምክንያት በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያጋጥመውን ጉዳት ለመቅረፍ በተለይም በህፃናት ላይ የሚከሰት መቀንጨርና የመቀጨጭ ችግርን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ተመልክቷል።
የክልሉን ማኀበረሰብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም የሥርዓተ-ምግብ መርሆዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተጠቁሟል።
የምግብ እና ኒውትሪሽን ፖሊሲንና ስትራቴጂ እንዲሁም የሰቆጣ ቃል-ኪዳንን በክልል ደረጃ በአግባቡ በመተግበር በክልሉ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፤ ለዜጎች ጤና መረጋገጥና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል ተቋማዊ አሠራርን ከክልል እስከ ታችኛው የቀበሌ መዋቅር ድረስ ለመዘርጋት የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት ያካተተ ደንብ መሆኑን ተገልጿል።
መስተዳድር ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ከዛሬ ነሀሴ 19 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ ሰራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ውሳኔ አስተላልፋል።

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top