የሀረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ነስሪ ዘከሪያ ለክልሉ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ በሰጡት መግለጫ በክልሉ የመስቀል ደመራ በአል በሰላም እንዲከበር ለማስቻል በቂ ቅድመ-ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
የበአሉን ፍፁም ሰላማዊነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀ ስራ እየተካሄደ ስለመሆኑ ያመላከቱት ምክትል ኮሚሽነር ነስሪ የመስቀል ደመራ በሚከበርበትና በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ቋሚ፣ ተንቀሳቃሽና ስውር የፀጥታ አካላት መመደቡንም ጨምረው ገልፀዋል።
በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል የፀጥታ እቅድ ወጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው ለሁሉም ፈፃሚና አባላት እንዲሁም አጋዥ ተቋማት የበአሉን አከባበር በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የማድረግና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸዉን ገልፀዋል።
በዚሁም ለበአሉ ሰላማዊነት ከክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሀገር መከላከያ ምስራቅ ዕዝ የፀጥታ ሀይሎች፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከሰላም አደረጃጀቶችና ከሌሎችም ባለድርሻዎች ጋር የጋራ የሆነ እቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መገባቱን ምክትል ኮሚሽነር ነስሪ አስታውቀዋል።
በዓላቱ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን አመራሮቹ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
መስከረም 15/01/2017