የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የውስጠ ፓርቲ የአመራር ግምገማ ማካሄድ ጀመረ

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመታዊ የአመራር የውስጠ ፓርቲ ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል

በግምገማ መርሃ ግብሩ መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ብልፅግና ፓርቲ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ትልቅ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ ይገኛል ።

በተለይም አመራሩ በስናምግበሩ የታነፀ በእውቀት፣ በክህሎትና በአፈፃፀም ብቃቱ የላቃ አመራር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን አንስተዋል።

ከዚህ አንፃርም ከውስጠ ፓርቲ ግምገማና ምዘና ግምገማው አመራሩ የአመለካከትና የተግባር አንድነት በመፍጠር፣ ሃላፊነቱን በብቃት በመወጣት የመሪነት ስብዕናና ስነ ምግባር ከመላበስ በፓርቲው በተጣለበት ግዴታን በአግባቡ ለመወጣት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል ።

አሳታፊ፣ ፍትሃዊና ግልፅ የሆነ ግምገማ በማድረግ ለቀጣይ ተልእኮ መነሳሰት የሚፈጥር ከመሆኑም በተጨማሪ የፓርቲ ዲሲፕሊን በማጎልበት የአመራር አንድነት የሚፈጠርበትና ለህዝቡ ለውጥ ሊያማጣ የሚችል ይሆናል ብለዋል።

አመራሩ በእቅድ የተያዙ ጉዳዮችን ከመፈፀም እና ከማስፈፀም አኳያ የተገኙ መልካም አፈፃፀሞችን እና ጉድለቶች የሚገመግምበትና ለህዝቡ ያመጣውን ለውጥ የሚለካበት ይሆናል ብለዋል።

በዚህ አመታዊ ግምገማ በበጀት አመቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮች እውቅና የሚሰጥበት ዝቅተኛ አፈፃፀም ያመጣ አመራርም የእርምት እርምጃ የሚወሰድበት እንደሚሆን ተናግረዋል።

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጃፈር ሱፊያን በበኩላቸው በግምገማው ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባበት ላይ የሚደረስበት ምዘና ይሆናል ብለዋል

አመራሩ በበጀት አመቱ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም እና የነበሩ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ከማስቀጠል አንፃር ግምገማው ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በዛሬው እለት የተጀመረው የአመራር ግምገማና ምዘና ለ 3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top