የሐረሪ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሀይማኖት የጋራ የሰላም እሴት እና ሴኩላሪዝም አስመልክቶ የተዘጋጃ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል
በሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና በሐረሪ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዘጋጅነት በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ፡፡
የሃይማኖት ተቋማት አብሮነት እና መቻቻል በአብሮነት ላይ ያለው ሚና እና ሴኩላሪዝም በሚል ርዕስ ለሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የዕምነት አባቶች ግንዛቤ ተሰጥቷል፡፡
በሐረር ክልል የህብረተሰቡን ባህላዊ አብሮነት እና የሃይማኖት አንድነት ለማስቀጠል የሃይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም በመግለጽ በቀጣይም በክልሉ የተለያዩ ሃይማኖታዊ በዓላት ሲከበር ሁሉም የኃይማኖት ተከታዮች በአንድነት እንዲቆሙ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶውፊቅ መሀመድ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ህዳር 26/2017




