የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የክረምት በጉ ፍቃድ መርሀግብር አገልግሎት ምክንያት በማድረግ በሐኪም ወረዳ ያስገነባቸውን ቤት በዛሬው እለት አስመረቆ አስረክበዋል።

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የክረምት በጉ ፍቃድ መርሀግብር አገልግሎት ምክንያት በማድረግ በሐኪም ወረዳ ያስገነባቸውን ቤት በዛሬው እለት አስመረቆ አስረክበዋል።

በቤት ርክክቡ ወቅትም የሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሐላፊ አቶ ቶፊቅ መሐመድ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን የኮሚሽኑ ከፈተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሊያስ ዩኒስ በተገኙበት የቤት እድሳት ለተደረገላቸው ግለሰቦች ርክክብ ተደርጎላቸዋል።

የሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሐላፊ አቶ ቶፊቅ መሐመድ እንደተናገሩት ከዚ ቀደም ይህን ቤት አውቀዋለሁ የፈረስ እና ለመኖርያ ምቹ ያልሆነ መሆኑን ስለማውቀው ፖሊስ ኮሚሽን ትክክለኛ ምርጫ ነው ። ዛሬ ላይም በዚህ መልኩ ሲያምር ማይት ደስ የሚል ነው። በዚህ ተግባር የተሰማራችሁ ሁሉም ለማመስገን እወዳለሁ ያሉ ሲሆን አክለውም እንደተናገሩት የክልሉን ሠላም በአስተማማኝ መንገድ ከመጠበቅ ጎን ለጎን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ፖሊስ ኮሚሽን እየተገበራቹ ነው። የተጀመረውን ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል ።

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንደተናገሩት ቀደም ሲል ይህ ቤት ምን እንደሆነ ይታወቃል አሁን ላይ ቤቱ በዚ ደርጃ ተሰርቶ ሲታይ ከምንም በላይ የቤቱ ባለቤቶች ቤቱ ታድሶላችው ከነበረው ከፈተኛ ችግር ወተው በእዚህ ስሜት ውሰጥ ሲገኙ ከእዚህ በላይ ደስታ የሚፈጥር እና ስሜትን የሚገዛ ጉዳይ የለምና በርግጥም የፖሊስ ተቀዳሚ ስራው ለማህበረሰቡ ስላም እና ደህንነት መጠበቅ ነውእና ሀላፊነት ወስደን ከመደበኛ ስራዎች ውጪ ጎን ለጎን ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚለው የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች ተወስዶ የተስራ መሆኑ ገልፀዋል ።

ኮሚሽኑ አቀማችው ዝቅተኛ የሆኑትን እና የገቢ ምንጭ የሌላቸውን የማህበረሰብ ክፍል በመዳሰስ የወገን አሌኝታ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል ።

አገራችን ካሉን አኩሪ እሴቶች መካከል የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህላችንን በማጠናከር ኮሚሽኑ የህንን አኩሪ እሴት በመጠበቅ ለማህበረሰቡ እየደረሰ ኮሚሽኑ የህንን መስል በጎ አድራጎት ስራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል ።

የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሊያስ ዩኒስ በበኩላቸው በሐኪም ወርዳ በፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ ስራዊት ጉልበት እና አቅም የተስራው ቤት በይበልጥ መንግስታችን ሰው ተኮር መሆኑንን እና ድሆችን የሚነቅፍ ሳይሆን የሚያቅፍ ከደሀው ጋር መለወጥ እንችላለንን ብሎ የሚያምን መንግስት መሆኑን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም የቤት እድሳት የተደረገላቸው እንደተናገሩት ፖሊስ የህዝብ አሌኝታ መሆኑን አረጋግጦልናል ስለተደረገልንም ሁሉ እጅግ እናመሰግናለን ሲሉ ተናገረዋል ።

Harari Police Commission

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top