የመስተዳድር ምክር ቤቱ የኮሪደር ልማቱን ዘላቂነት የሚያረጋግጥ ደንብ አፀደቀ
ሀረር ነሀሴ 22/2016(ሀክመኮ):- የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የኮሪደር ልማቱን ዘላቂነት የሚያረጋግጥ ደንብ አፀደቀ።
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ (ካቢኔው) የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤትን እንደገና ለማቋቋም እና አደረጃጀቱን፣ ሥልጣንና ተግባራቱን ለማሻሻል በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ተወያይት ደንቡ ስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።
ፀድቆ ወደ ስራ የገባው ደንብ በከተማው እየተስተዋሉ የሚገኙ የደንብ መተላለፎችንና ተያያዥ ሕገ-ወጥ ተግባራትን በዘላቂነት ለመከላከል ብሎም እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ቅጣትን በመወሰን አግባብ ባላቸው ሕጎች የተመላከቱ የደንብ መተላለፍ ቅጣቶችን በማስፈፀም የከተማዋን ፅዳትና ውበት ለማስጠበቅ እና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ለማድረግ የሚያግዝ ነው።
ደንቡ በከተማው ኮሪደሮች፤ መንገዶችና ተጓዳኝ ልማቶች የሚሰጡትን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለማስጠበቅ የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከዛሬ ነሀሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስናል።




All reactions:
Ahmed Mohammed Abdukrim Ali, Mohammed Abdi Kalid and 49 others