መስከረም 30/2017
በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ከመጡ አመራሮች ጋር በሀገር ደረጃ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በተካሔደው 7ኛው የፀጥታ አካላት የምክክር መድረክ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም የእምርታ ዘመን እናደርገዋለን በሚለው መሰረተ-ሀሳብ ላይ መግባባት ላይ መደረሱ ይታወቃል ሰለሆነም መግባቢያውን መሰረት በማድረግ በክልላችን በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ከመጡ አመራሮች ጋር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በተገኙበት መድረክ ከቢሮ ዳይሬክተሮች ጋር በመመካከር የሚታዩ የጋራና የተናጠል ክፍተቶችን በቅደም ተከተል በመለየት የተዘጋጀ ሰነድ በማቅረብ አስፈላጊውን ድጋፍ ከማን ምን ይጠበቃል በሚል በስፋት ውይይት የተደረገና መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቋል ፡፡



ሰላም ለሁሉም !!!!!
ሁሉም ለሰላም !!!!!
ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙሊኬሽን