በዓሉ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሀሳብ በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሲከበር
የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በየዓመቱ መከበሩ ለብሔራዊ አንድነት፣ ለሉዓላዊነትና ለኢትዮጵያ ከፍታ ቀጣይነት ብሔራዊ መነቃቃትን ለመፍጠር ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው የተናገሩት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አት ቶፊቅ መሀመድ ለሀገርና ለሰንደቅ ዓላማ ያለንን እውነተኛ ክብርና ፍቅር ሁላችንም የምንገልፅበትና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ዳግም ቃላችንን የምናድስበት ዕለት ይሆናል ሲሉም ገልፀዋል።
አክለውም በደምና አጥንት ተጠብቆ የቆየውን የሰንደቅ ዓላማችን ክብርና ሉዓላዊነታችንን ይበልጥ ማፅናት የሚቻለው በተሰማራንበት የሥራ መስክ ተግባራችንን በትጋት ስናከናውን ነው




በተለይ በክልላችን ሰላማችንን አጽንተን ለመቀጠል ያለንን ቁርጠኝነት ስናረጋግጥ እንዲሁም በኅብር ተናብበን መኖር ስንችል ብቻ ነው በማለት አፅንኦት ሰጥተው መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን
በመረሃ ግብሩ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊ ኮሚሽነር ነስሪ ዘከርያ የቢሮው መላው ሰራተኛ በተገኘበት በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ሰንደቅ አላማ የመስቀል መርሃ ግብር ተካሄዶ ተጠናቋል ።
ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን