በሐረሪ ክልል የብልፅግና ፖርቲ 5ተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አሰመልክቶ በለፍት አምስት አመታት ፓርቲው ያስመዘገበውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎችን የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት ለእይታ ቀርበዋል።
በሐረሪ ክልል 5ኛ ዓመት የብልፅግና ፓርቲ ምስረታ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት የፓርቲው ምስረታ በዓል በአሚር አብዱላሂ አደራሽ የፎቶ ኤግዚቪሽን በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በክብርት ሮዛ ኡመር እና የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በክቡር አቶ ጌቱ ወዬሳ በጋራ በመሆን ተከፍቷል፡፡
ያለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ የመንግስት ተቋማት ስኬቶችን የተመለከተ የፎቶ ኤግዚቪሽን ቀርቧል፡፡
በኤግዝብሽኑ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጃፈር ሱፊያንን ጨምሮ የክልል እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።





All reactions:
21Abdo Ziyad, Tofik Mohammed Yuyo and 19 others