የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በማጎልበት የክልሉን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል ርብርብ ይደረጋል- አቶ ጌቱ ወዬሳ

የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በማጎልበት የክልሉን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል ርብርብ ይደረጋል- አቶ ጌቱ ወዬሳ

የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በማጎልበት የክልሉን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል ርብርብ እንደሚደረግ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ለውጥ አምጭ እሳቤዎችን በመላበስና በመተግበር ፣ የህዝቡን የአብሮነት እና የመረዳዳት እሴቶችን በማዳበር ፣ ሰላምን በማስፍን እና ህዝቡን ለልማት ስራዎች በማስተባበር በሁሉም ዘርፎች አንፀባራቂ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

ፓርቲውን በአስተሳሰብ ፣ በአደረጃጀት እና በተልዕኮ አፈፃፀም የማጠናከሩ ስራ ጥሩ መሻሻል ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ኃላፊው አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት በመረባረቡ ብሎም የህዝቡ ንቁ ተሳትፎ እና የተደረጉ ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ለተመዘገበው ውጤት ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ገልፀዋል።

በተጀመረው የ2017 በጀት ዓመትም አባላትንና ህዝቡን በማሳተፍ የተጀመሩ አበረታች ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ርብርብ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

በክልሉ በተከናወኑ የልማት ስራዎች ከተመዘገቡ ስኬቶች ባሻገር አባላት ህዋሳትን የመተጋገያ መድረክ በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ እመርታዊ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የተጀማመሩ ጥረቶችን ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በቀጣይም ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት የተጀመረው ጥረት ግለቱን ጠብቆ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ጠንካራ የፓርቲ ተቋም መፍጠር፣ የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን እና የአሰራር ግልጽነትን ማስፈን እንዲሁም የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በማበጀት በኩል በተደረገዉ ጥረት የተመዘገበውን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም በአጽንኦት ተናግረዋል።

በ2017 በጀት ዓመትም የፓርቲውን መዋቅር በማጠናከርና እሳቤውን በተገቢው መንገድ በማስረጽ በክልሉ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ሁለተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ይከወናሉ ብለዋል።

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top