የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል፦ አቶ አሪፍ መሃመድ

የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል ሲሉ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ ገለፁ።

ዘንድሮ የሚከበረው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር የብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሀረሪ ክልል በድምቀት ለማክበር ከበዓሉ አቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ የዘንድሮውን የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ሀገራዊ መግባባትና አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር ገልጸዋል።

በዓሉ የህዝቦች የአብሮነትና የመቻቻል በዓል እንደመሆኑ በይበልጥ በሚያጠናክር ብሎም የክልሉን ልማትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በሚያጎለብቱ መርሐግብሮች እንደሚከበር ነው የተናገሩት።

የብሄር ብሄረሰብ ቀን መከበሩ በተለይም እንደ ሀገር አንድነትን ለማጎልበት የጋራ ትርክትን ለመገንባት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

በዚህም መሠረት በበዓሉ ወቅት ሲምፖዚየም፣ የጥያቄና መልስ ውድድሮች፣ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የሙዚየም ጉብኝቶች፣ የስነጽሁፍ ዝግጅቶች ባህላዊ ትርኢትና ጭፈራዎች፣ ሰብል በመሰብሰብና በሌሎች መርሃግብሮች ይከበራል ብለዋል።

በመድረኩም የበዓሉ አከባበርን በተመለከተ ዝርዝር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩም የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሃመድ፣ የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘንድሮ የሚከበረው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር የብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ”ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

All reactions:

5Abdo Ziyad and 4 others

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top