የሀረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እንደገለፁት በቁልቢ ገብርኤል ከተከበረው አመታዊ የንግስ በአል በተጨማሪ በሀረር ከተማ አራተኛ ገብርኤል የተከበረው በአልም ፍፁም ሰላም በሰፈነበት መልኩ ተከብሮ በሰላም መጠናቀቁን ጠቁመዋል።
በአሉ በሰላም መጠናቀቁ ሀረር የሰላም፣ የፍቅርና የመቻቻል ከተማ መሆኗና ህዝቦቿም ሰላም ወዳድ መሆናቸውን አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉት የክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለፌዴራል ፖሊስ፣ ለሰላም አደረጃጀቶች፣ ለአጎራባች ክልል ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ መዋቅሮችና ለሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብም አቶ ቶፊቅ መሀመድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።