በዛሬው እለት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አና የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የማሰረታዊ ደርጅት አመራሮችና ሰራተኞች “የጠንካራ ፓርቲ ግንባታና በህዝብ ንቅናቄ ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ጉዟችን “በሚል መሪ ሀሳብ በልሳነ ብልጽግና መጽሔት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበው በዝርዝር ተወያይተዋል።
በመድረኩ በዋናነትም የተቋማትን አቅም በማሳደግ የማህበረሰብ ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ አና በየተቋማቱ የሚስተዋሉ የመልካም አስተደደር ችግሮችን በመፍታት ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ መሆኑ በመግለፅ ጠንካራ የፓርቲ ግንባታ የማስቀጠል ስራችው ለማጠናከር የልሳነ ብልፅግና ዕትም ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዟችንን ለማፋጠን ጉልህ ሚና እንዳለው ተገልፁዋል።


