በሀረር ከተማ ኢማም አህመድ አልጋዚ መስኪድ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ተፈቷል- ሼክ አብዱሰላም ጂብሪል
ሀረር መስከረም 29/2017(ሀክመኮ):- በሀረር ከተማ ኢማም አህመድ አልጋዚ መስኪድ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ አብዱሰላም ጂብሪል አስታወቁ። በሀረር ከተማ በተለምዶ አራተኛ መስጂድ ተብሎ በሚጠራው የኢማም አህመድ አልጋዚ መስጂድ ከሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። […]