በሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ሁነቶች ማክበር ጀመረ ።

በሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ሁነቶች ማክበር ጀመረ ።

የሐረሪ ክልልብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ” በህብር ወደ ኢትዮጽያ ልዕልና ” በሚል መሪ ሃሳብ የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ማክበር ጀምረዋል ።

በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ፓርቲው በአምስት አመታት ውስጥ ያስመዘገባቸው የለውጥ ትሩፋቶችን የሚያስቀጥል የፓናል ውይይት በማካሄድ እያከበረ ይገኛል።

ብልፅግና በተግባር የተፈተነ ቃሉን የኖረ ተራማጅ ፓርቲ ነው። ሀገራችንን ከድህነት አረንቋ በማውጣት ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ቀን ከሌት የሚተጋው ፓርቲያችን በርካታ ታሪካዊ ስብራቶችን እየጠገነ ሀገራችንን በፅኑ የህብረብሔራዊ አንድነት መሰረት ላይ እየገነባ ይገኛል።

የአመራሩን እንዲሁም የአባላትን የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት እየገነባ በአዲስ እሳቤ አዳዲስ ስኬቶችን እያስመዘገበ የሚገኘው ብልፅግና በቀጣይም ህልሞቹን እውን በማድረግ ዕመርታዊ ድሎችን ለማስመዝገብ እና የነበሩ ክፍተቶችን ለማረም የአምስት ዓመታት ጉዞውን እየዘከረ ነው፡፡

ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችንን የፖለቲካ ስብራት በመጠገን ከመገፋፋት በማውጣት የጋራ ሀገራችንን በትብብርና በአብሮነት መገንባት የሚያስችል መሰረት የጣለ ፓርቲ ነው።

የፖለቲካ ምህዳሩን ያሰፋው ፓርቲያችን የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲንም በማዳበር ባሉት ከፍተኛ የአባላት ቁጥር የሀገር ግንባታ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝና ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ አቅምም እንዳለው ባለፉት አምስት ዓመታት በተግባር አሳይተዋል ።

በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን በማስረፅ ሀገራችንን በፅኑ መሰረት ላይ እንድትገነባ እየተጋ ይገኛል።

ሐረር ከተማ ውብና የቱሪዝም መደረሻ እንድትሆን እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ የህዝባችንን አኗኗር እያሻሻለ ያለው የኮሪደር ልማታችን ለትራንስፖርቱ ዘርፍ መዘመን በተጨማሪ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ ነው።

ፕሮግራሙ የፓርቲያችንን የአምስት ዓመት ጉዞ የሚዘክሩ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

All reactions:

47Hasan Adam, Kubeybi Ahmed Sĩřåĵ and 45 others

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top