ፓርቲያችን ብልፅግና ባለፉት 5 ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶችን በውጤት አጅቦ ለማስቀጠል ይሰራል- ወይዘሮ ሮዛ ኡመር

ፓርቲያችን ብልፅግና ባለፉት 5 ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶችን በውጤት አጅቦ ለማስቀጠል ይሰራል- ወይዘሮ ሮዛ ኡመር

በሀረሪ ክልል ባለፉት 5 ዓመታት የብልፅግና ጉዞ የተመዘገቡ ስኬቶችን በውጤት አጅቦ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ባለፉት 5 ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን እና የጥያቄና መልስ ውድድር 5ተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው።

በምስረታ በዓሉ ላይ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር እንደገለፁት ፓርቲው ባለፉት 5 ዓመታት ጉዞው ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግቧል።

ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል ዕውን በማድረግ በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ፓርቲው እራስን በምግብ ለመቻል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሲያከናውናቸው የቆዩ ኢንሼቲቮች የምግብ ዋስትናን እያረጋገጡ እንደሚገኙም አስገንዝበዋል።

በተለይ ኢንሼቲቩ ፆም ያድር የነበረውን መሬት በማልማት ከውጭ አገራት ይገባ የነበረውን የስንዴ ምርት በማስቀረት በአገር ውስጥ በመተካት የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ አገራት በመላክ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመዋል።

በተለይ ፓርቲው ለሰው ተኮር ስራዎች በሰጠው ትኩረት በክረምት ወራት የተሰራው የበጎ ፈቃድ ስራ የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮነሚያዊ ጫና የቀነሰ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሀገሪቱን እድገት እና ብልፅግና ለመጪው ትውልድ ማስቀጠል የሚችል ለአየር ንብረት ለውጥ ተመራጭ የሆነ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ የምግብ ዋስትናን በማሻሻል፣ የባዮዳይቨርሲቲ ሀብትን በማጎልበትና በረሃማነትን ለመዋጋት የሚያስችል ውጤት የተመዘገበበት መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይ ፓርቲው የመለያየት ፖለቲካን በማስቀረት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጎልበት በህዝቦች መካከል የወንድማማችነት እሴት እንዲጎለብት እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እንዲሰፍን ማስቻሉን አስገንዝበዋል።

በተለይ ሀረር የረጅም ዓመት እድሜ ቢኖራትም ስሟን የሚመጥን ዕድገት ሳይመዘገብ መቆየቱን በማስታወስ ፓርቲው ከተማዋን የሚመጥን ዕድገትን ዕውን ለማድረግ ባከናወናቸው ስራዎች የከተማዋን የቀድሞ ምልከታ መቀየር መቻሉን አስገንዝበዋል።

በገጠርና በከተማ ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ስራ መስራት መቻሉን ተናግረዋል።

ፓርቲው ባለፉት አመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በውጤት አጅቦ በማስቀጠል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር አረጋግጠዋል።

በመርሀ ግብር ላይ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ጨምሮ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል።

+14

All reactions:

52You, Abdo Ziyad, Tofik Mohammed Yuyo and 49 others

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top