ሰብአዊነትን በማስቀደም ሴቶችንና ህጻናትን ከጥቃት መከላከል እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ ።
“የሴቷ ጥቃት የኔም ጥቃት ነው ዝም አልልም” በሚል መርህ የጸረ ጾታዊ ጥቃትን መከላከል ቀን በሐገር አቀፍ ደረጃ ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 በተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተካሄደ ይገኛል።
“የሴቷ ጥቃት የኔም ጥቃት ነው ዝም አልልም” በሚል መርህ የጸረ ጾታዊ ጥቃትን መከላከል ቀን በሐገር አቀፍ ደረጃ ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 በተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተካሄደ ይገኛል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የሐረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መግለጫ ሰጥተዋል።
የሐረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እንደገለፁት የሚፈለገውን የሐገር ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ከጥቃት መከላከል እንደሚገባ ገልጸዋል።
እንደ ሀገር የተጀመረው ብልፅግና እውን ለማድረግ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ያሉት ሀላፊው ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ና ሚናቸውን ማጉላት ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም በሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት ለማስቆም እንደ ክልል የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

All reactions:
72Eliyas Abdurhman, Nasradiin Juhar and 70 others