Author name: admin

Selam, ለሰላም, ዜና, የሰላም እና ደህንነት

ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ ነው -አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ጥቅምት 5/2017(ሀክትቢ):- በሀረሪ ክልል ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ። የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እና የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዕውቅና ሽልማት መርሀ ግብር አካሂዷል። በመርሀ ግብሩ ላይ በአገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና […]

Selam, ለሰላም, በጎ ፈቃድ, ዜና

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ኃላፊነታችንን ለመወጣት ቃላችንን በማደስ መሆን አለበት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር

በዓሉ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሀሳብ በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሲከበር የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በየዓመቱ መከበሩ ለብሔራዊ አንድነት፣ ለሉዓላዊነትና ለኢትዮጵያ ከፍታ ቀጣይነት ብሔራዊ መነቃቃትን ለመፍጠር ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው የተናገሩት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አት ቶፊቅ መሀመድ ለሀገርና ለሰንደቅ ዓላማ ያለንን እውነተኛ ክብርና ፍቅር ሁላችንም የምንገልፅበትና በሰንደቅ ዓላማ

Selam, ለሰላም, ዜና

በሀረሪ ክልል “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 17ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬው ዕለት ይከበራል፡፡

በሀረሪ ክልል “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 17ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬው ዕለት ይከበራል፡፡ ዘንድሮ በክልል ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በክልል ደረጃ በድምቀት ይከበራል። ዛሬ ከረፋዱ 4:30 ሠዓት ላይ በሀረሪ ክልል በሚገኙ ሁሉም መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል

Selam

በሰላምና ፀጥታ እስተዳደር ቢሮ ከክልሉ የመጅሊስ አመራሮችና ከኃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ውይይት ተደረገ

በሰላምና ፀጥታ እስተዳደር ቢሮ ከክልሉ የመጅሊስ አመራሮችና ከኃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ውይይት ተደረገ========================= ጥቅምት 3/2017 በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከክልሉ የመጅሊስ አመራሮች ፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ከሁሉም ወረዳ የጁምአ መስኪድ ኢማሞች፣ሼኮች ፣አባገዳዎች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እና በአራተኛ መስኪድ ተፈጥሮ የነበረው ችግር መንስኤና በሰላም መጠናቀቅ ላይ ያተኮረ ውይይት በስፋት የተደረገ ሲሆን በመድረኩም የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር

Selam, ለሰላም, ዜና, የሰላም እና ደህንነት

የፕላን ሚኒስትሯ በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመለከቱ

የፕላን ሚኒስትሯ በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመለከቱ ሀረር ጥቅምት 2/2017(ሀክመኮ):- የኢፌድሪ ፕላን ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ሚኒስትሯ ከሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጋር በመሆን ነው በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱት። በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት፣ የኢኮ ፓርክ፣ የአርሶ አደሮች ምርት

Selam, ለሰላም, መግለጫዎች, ዜና

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ከመጡ አመራሮች ጋር ውይይት አደረገ

መስከረም 30/2017 በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ከመጡ አመራሮች ጋር በሀገር ደረጃ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በተካሔደው 7ኛው የፀጥታ አካላት የምክክር መድረክ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም የእምርታ ዘመን እናደርገዋለን በሚለው መሰረተ-ሀሳብ ላይ መግባባት ላይ መደረሱ ይታወቃል ሰለሆነም መግባቢያውን መሰረት በማድረግ በክልላችን በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ከመጡ አመራሮች ጋር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ

Selam, ለሰላም, መግለጫዎች, ዜና, የሰላም እና ደህንነት

በሀረር ከተማ ኢማም አህመድ አልጋዚ መስኪድ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ተፈቷል- ሼክ አብዱሰላም ጂብሪል

ሀረር መስከረም 29/2017(ሀክመኮ):- በሀረር ከተማ ኢማም አህመድ አልጋዚ መስኪድ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ አብዱሰላም ጂብሪል አስታወቁ። በሀረር ከተማ በተለምዶ አራተኛ መስጂድ ተብሎ በሚጠራው የኢማም አህመድ አልጋዚ መስጂድ ከሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

Selam, ለሰላም, ዜና

በሀረሪ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ ከ114 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ስራ ተከናውኗል- አቶ ጌቱ ወዬሳ

በሀረሪ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደረገና ከ114 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የበጎ ፍቃድ ስራዎች መከናወኑን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ። ኃላፊው ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች በሚመለከት እንደተናገሩት በክልሉ በበጎ ፍቃድ የሚከናወኑ ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ይገኛል። የሚከናወኑ ስራዎችም በተለይ

Selam, ለሰላም, ዜና

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጥምር የፀጥታ ኮሚቴ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ተወያየ

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ አካሉ በቅንጅት በመሥራት በክልላችን የተከበረውን ሀይማኖታዊ የመስቀል ደመራ በአል በሰላም መጠናቀቅ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ለተሰራው ሥራ ምስጋና የተሰጠበትና በቀጣይም በክልላችን ብሎም በከተማችን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ የፀጥታው ጥምር ኃይል ከወትሮው በበለጠ መሥራት እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠሲሆን በመድረኩ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እና የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን

Selam, ለሰላም, ዜና

በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአንደኛው ሩብ አመት የሪፖርት አፈፃፀምና የ11ኛው ዙር የብሄራዊ በጎ ፍቃድ ወጣቶች ምዝገባ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ተገመገመ

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአንደኛው ሩብ አመት የሪፖርት አፈፃፀምና የ11ኛው ዙር የብሄራዊ በጎ ፍቃድ ወጣቶች ምዝገባ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ከቢሮ የማኔጅምንት ፣ቡድን መሪዎች እና የዘጠኙም ወረዳ የፀጥታ አስተባባሪዎች ፣የሚሊሻ ዴስክ በጋራ በመሆን ተገመገመ ፡፡ በአንደኛው ሩብ አመት የተሰሩ ስራዎች ያጋጠሙ ችግሮችና የወደፊት አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ

Scroll to Top