በሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ “የመስቀል ደመራ በዓል በማስመልከት የፅዳት መርሃ ግብር ተከናወነ
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች ፣የፖሊስ ኮሚሽን አባላት ፣የወረዳ ሰላም አደረጃጀቶች፣ የሀይማኖት አባቶች በጋራ በመሆን የሀረርን የአብሮነት እሴት በሚገልፅ መልኩ የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በሚከበርበት ቦታ የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል። በዚህ የጽዳት ዘመቻ ላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ከሙስሊም እምነት አባቶችና ወንድሞች ፣ከፕሮቴስታንት እምነት አባቶች በጋራ የመስቀል ደመራ በአል ሀይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ […]