አጠቃላይ የፀጥታ ስራና የክረምት በጎ አገልግሎት መርሐ ግብር ከሐምሌ 1 እስከ ነሀሴ 15/2016 ያለው የሥራ አፈፃፀም ተገመገመ

የሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በተገኙበት ከክልል የተመደቡ ባለሞያዎች ፣የዘጠኙም ወረዳ የሰላምና ፀጥታ አስተባባሪ እና ሚሊሻ ዴስክ አጠቃላይ የፀጥታው ስራ እና የክረምት በጎ አገልግሎት መርሐ ግብር ከሐምሌ 1 እስከ ነሀሴ 15/2016 ያለው የሥራ አፈፃፀም በተሰጠው ቼክ ሊስት መሠረት የነበሩ ጠንካራ ጎን የታዩ ክፍተቶችን ተገምግመዋል።

እንዲሁም በቀጣይ በታዪ ክፍተቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራና ፀጥታውን የሚመሩ አስተባባሪዎች የፀጥታ ሥራና አብሮነትን የማጠናከር ሥራ እንዲሰራ እና በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የፊታችን አርብ ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የሰላም አደረጃጀቶቻችን በንቃት እንዲሳተፉና መርሃ ግብሩ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዳጠናቀቅ አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ የሀረሪ ክልል ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ መሐመድ በቀጣይ የሥራ አቅጣጫ እና ተልእኮ በመሥጠት ተጠናቋል።

ዘገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top