የአረንጓዴ አሻራ መርዐ-ግብር የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ክፍተኛ የስራ ሐላፊዎችና ነዋሪዎች በኤረር ወረዳ ጀበርቲ ተራራ ላይ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ እንደገለፁት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል ።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተፅእኖ ለመቆጣጠርና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል ።
ሀገር የያዘችውን በአንድ ጀምበር 600ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሀግብ በክልሉ ከጠዋት ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ።
በክልሉም 350 ሺ ችግኞች በአንድ ጅንበር ለመትከል ግብ መያዙን ጠቁመው ከሚተከሉ ችግኞች እ 70በመቶው የምግብን ዋስትና የሚያረጋግጡ ሲሆኑ ቀሪው 30 በመቶው የደን ዛፎች መሆናቸውን አብራርተዋል ።