በሐረሪ ክልል መኸር እርሻ እስካሁን 11 ሺህ 774 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል
በሐረሪ ክልል የመኸር እርሻ ወቅት እስካሁን 11 ሺህ 774 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር እንደገለፁት በክልሉ በተለይም በአሁኑ ወቅት ፆም ሲያድር የቆየ መሬት ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ጭምር ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት ለመላቀቅ በቁርጠኝነት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህም የማዳበሪያ፣ የዘርና ሌሎች የግብርና […]